የአምባሳደሮቹ ሹመት ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ ላይ መሰረት አድርጎ የተሰጠ ነው-አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

71

ጥር 19 ቀን 2014 (ኢዜአ)በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተሰጠው የአምባሳደሮች ሹመት የአገርን ብሔራዊ ጥቅምና ገጽታ ለማስጠበቅ ሙያን መሰረት አድርጎ የተከናወነ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሰሞኑ በሰጡት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደሮችና የአምባሳደሮች ሹመት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና በዚሁ ወቅት በሳምንቱ የተከናወኑ አበይት ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ክንውኖችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ፣የአምባሳደሮች ሹመት ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገና ዲፕሎማሲያዊ ግብን ለማሳካት የሚያስችል ነው ብለዋል።

ሹመቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እያከናወነ ያለው የሪፎርም አካል መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም