በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ታዳሚዎች ምቹና ቀልጣፋ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል

79

ጥር 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለሚታደሙ እንግዶች ምቹና ቀልጣፋ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

35ኛው የአፍሪካ ሀብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ከመሪዎቹ ጉባኤ ቀደም ብሎ ጥር 25 እና 26 የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ የሚካሄድ ይሆናል።

በመሆኑም በጉባኤው ላይ ለሚታደሙ እንግዶች ፈጣንና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል።

የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሙሉነህ አቦዬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት ቢሮዎች አሉ።

በኤሌክትሮኒክስ ካርድ መገበያየት ለሚሹ እንግዶችም በሆቴሎችና በሚያርፉባቸው ቦታዎች የግብይት ማሽን (ፖስ ማሽን) ተዘጋጅቷል ብለዋል።

የባንኩ ቅርንጫፎች የተቀላጠፈ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል።

በመሆኑም ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶች በተጠቀሱት አማራጮች የተቀላጠፈ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም