በተሽከርካሪ አደጋ የሁለት ሰው ህይወት አለፈ

136

ነገሌ፣ ጥር 18/2014/ኢዜአ/ በምእራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ሳጂን ፈዬራ ከይረዲን ለኢዜአ እንደገለፁት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -43687 አ.አ የጭነት ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -17064 ደህ ከሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

በአደጋው የህዝብ ማመላለሻው አሽከርካሪና ረዳቱ ህይወታቸው ወዲያው ማለፉን ተናግረዋል።

የአካል ጉዳት የደረሰበት የጭነት መኪና አሽከርካሪ በቡሌ ሆራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአደጋው ሁለት የቤት እንስሳትም መሞታቸውን የገለጹት ዋና ሳጂን ፈዬራ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን አስታውቀዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም