ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለ27 አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ

109

ጥር 18 /2014 (ኢዜአ)ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለ27 አምባሳደሮች ሹመት መስጠታቸውን የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ፕሬዝዳንቷ የሰጡት አስራ ስድስት ባለ ሙሉስልጣን አምባሳደር  እንዲሁም አስራ አንድ የአምባሳደርነት ሹመት ነው፡፡

በዚሁ መሰረት

1 አቶ ተፈራ ደርበው፣

2 አቶ ደሴ ዳልኬ ፣

3 ዶክተር ስለሺ በቀለ ፣

4 ጀነራል ባጫ ደበሌ ፣

5 ጀነራል ሀሰን ኢብራሒም ፣

6 ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ ፣

7 ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ ፣

8 አቶ ረሻድ መሀመድ ፣

9 አምባሳደር ጀማል በከር ፣

10 አቶ ፈይሰል አሊይ ፣

11 አቶ ኢሳያስ ጎታ ፣

12 አቶ ጸገአብ ክበበው ፣

13 አቶ ጣፋ ቱሉ ፣

14 ዶክተር ገነት ተሾመ ፣

15 አቶ ዳባ ደበሌ እና

16 አቶ ፈቃዱ በየነ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡

እንዲሁም :-

1 አቶ አሳዬ አለማየሁ፣

2 አቶ ሃይላይ ብርሃነ፣

3 አቶ አወል ወግሪስ፣

4 ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት፣

5 አቶ አንተነህ ታሪኩ፣

6 አቶ አክሊሉ ከበደ፣

7 አቶ ሰይድ መሐመድ፣

8 አቶ ዮሴፍ ካሳዬ፣

9 አቶ ዘላለም ብርሃን፣

10 ወይዘሮ ፍርቱና ዲባኮ እና

11 አቶ ወርቃለማሁ ደስታ

በአምባሳደርነት መሾማቸውንም የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ለኢዜአ አስታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ ሹመቱን የሰጡት በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም