ኢትዮጵያ፣ ጂቡቲና ሩሲያ የጋራ የቢዝነስ ፎረም አካሄዱ

104

ጥር 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) “የሩሲያ፣ ኢትዮጵያና የጂቡቲ የጋራ የቢዝነስ ፎረም” ትናንት በሞስኮ ተካሂዷል።

ከአፍሪካ ጋር የሚደረጉ የኢኮኖሚያዊ ትብብሮችን የሚያሳልጠው ኮሚቴ እና የሩሲያ የንግድና ኢንዱስትሪ ማህበራት ናቸው ፎረሙን ያዘጋጁት።

የሦስቱም ሀገራት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የንግድና የዘርፍ ማህበራት እንዲሁም በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑን ጨምሮ ሌሎችም አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የንግድና የዘርፍ ማህበራት፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ማህበር ተወካዮች የየዘርፋቸውን ልምድና ተሞክሮ አቅርበዋል።

ፎረሙ ለሩሲያ አነስተኛና መካከለኛ የቢዝነስ ተቋማት በኢትዮጵያና በጂቡቲ ስላሉ የኢንቨስተመንት ምቹ ሁኔታዎች ግንዛቤ መፍጠርን ያለመ ነው ተብሏል።

ከዚህም ባሻገር የሁለትዮሽ የንግድና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮችን ለማሳደግ እንደሚያስችልም ተነግሯል።

በሩሲያ የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብሮችን የሚያሳልጠው ኮሚቴ ወደ ኢትዮጵያና ጂቡቲ የቢዝነስ ልዑካንን ለመላክ የአሁኑ ስብሰባ እንደመሸጋገሪያ እንደሚያገለግለው አሳውቋል።

በቅርቡም በሁለቱ ሀገራት የሩሲያን የቢዝነስ ተቋማት የሚደግፉ ማዕከላትን እንደሚያቋቁም መጥቀሱን ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም