ጉምሩክ ኮሚሽን ለኮንሶ ዞን ከ 24 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

84

ጥር 16 ቀን 2014 (ኢዜአ)የጉምሩክ ኮሚሽን በኮንሶ ዞን በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች 24.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች እና የግንባታ እቃዎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኮሚሽኑ በመንግስት ከተሰጠው ገቢን በብቃት የመሰብሰብ፣የወጭና የገቢ ንግድ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ ማድረግ፣ህገ ወጥ ንግድን እና ኮንትሮባንድን ከመከላከል ተልእኮው በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።

ድጋፉን ያስረከቡት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በኮንሶ ዞን በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም 24.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች፤አልባሳት እና የግንባታ እቃዎች ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

May be an image of 13 people, people standing and outdoors

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ጊዚያት 4.5 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ድጋፎቹ በተለያዩ ጊዜያት የህይወት እና የአካል መስዋዕትነት ተከፍሎባቸው የተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች በመሆናቸው ለተጎጅዎች በትክክል እንዲደርሱም ኮሚሸነር ደበሌ አሳስበዋል ።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው፤ በዞኑ በሰው ሰራሽ ችግሮች የተፈናቀሉ ከ80 ሺ በላይ ነዋሪዎች መኖራቸውን ገልጸው በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ማስረዳታቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም