ለ21ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የተካሄደው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
ለ21ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የተካሄደው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ
65
ጥር 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው 21ኛው የሩጫ ውድድር በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
የውድድሩ በሠላም መጠናቀቅ ኢትዮጰያ ሰላም አይደለችም የሚል መረጃ የሚያሰራጩ አካላት መረጃቸው ትክክለኛ ያልሆነና ሀሰተኛ መሆኑን ያረጋገጠ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ፤ ውድድሩ ከተማችን አዲስ አበባ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባትና መሰል ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ምቹ መሆኗን የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡
በመጪው ሳምንት ኢትዮጵያ 35ኛውን የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ የምታስተናግድ ስለሆነ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል።
የዛሬው ውድድር በሠላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡