የኢትዮጵያና ሱዳን ሕዝቦች ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ

107

ጥር 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) "የኢትዮጵያና ሱዳን ሕዝቦች ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ናቸው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ መግባታቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት "የኢትዮጵያና ሱዳን ሕዝቦች ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ናቸው" ሲሉ ገልጸዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሀም በላይ እና የብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

 በቆይታቸውም የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም