በኢትዮጵያ የነበረኝ ቆይታ ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ነገሮች ያወኩበትና የተማርኩበት ነው-ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

116

ጥር 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) "በኢትዮጵያ የነበረኝ ቆይታ ስለኢትዮጵያ ብዙ ነገሮች ያወኩበትና የተማርኩበት ነው" ስትል ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ተናገረች።

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ በኢትዮጵያ የነበራትን ቆይታና በቀጣይ ልትሰራ ባቀደቻቸው ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥታለች፡፡

ጋዜጠኛዋ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ለማወቅ እንደመጣችና በቆይታዋም ብዙ ነገሮችን መማርና መረዳት እንደቻለች ገልጻለች፡፡

"በኢትዮጵያ የተመለከትኩት ነገር ወደ አሜሪካ ስመለስ ለቀጣይ ስራዎቼ ያግዘኛልም" ብላለች፡፡

አሁንም ከእውነት ጎን በመቆም የኢትዮጵያን ሁኔታ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳወቋን እንደምትቀጥል ተናግራለች፡፡

የ‘በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ እንቅስቃሴ በቀጣይ በተደራጀ መልኩ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ገልጻ፤ ለኢትዮጵያ በምትችለው አቅም ሁሉ ድጋፍ ማድረግዋን እንደምትቀጥል አረጋግጣለች፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም