በጋምቤላ ክልል የበጋ ወቅት የተፋሰስ ልማት ስራ በይፋ ተጀመረ

73

ጋምቤላ ፤ ጥር 13 ቀን 2014(ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል የበጋ ወቅት የተፋሰስ ልማት ዘመቻ በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን መንገሺ ወረዳ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

በዘመቻው ከ49 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተመልክቷል።

May be an image of 7 people, people standing, outdoors and tree

ከ250 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች በዘመቻው ይሳተፋሉ ተብሎም እንደሚጠበቅ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ለአንድ ወር የሚቆየው ዘመቻ ማስጀመሪያ ሥነ- ሥርዓት ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም