11 ሺህ ከረጢት የኢትዮጵያ ቡና በአምስት ሰከንድ ውስጥ ተሸጠ

90

ጥር 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) በቻይና በተካሄደ የቀጥታ ሽያጭ ስነስርዓት 11 ሺህ ከረጢት የኢትዮጵያ ቡና በአምስት ሰከንድ ውስጥ መሸጡን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

በሚኒስቴሩ የአፍሪካ ጉዳይ ጀኔራል ዳይሬክተር ዉ ፔንግ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት፤ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በተገኙበት የተካሄደው የቀጥታ ሽያጭ ሂደት ውጤታማ ነበር።

የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ውስጥ ፍላጎቱ እያደገ መምጣቱን የገለጹት ዉ ፔንግ፤ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ከጥር እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ወደቻይና የገባው የኢትዮጵያ ቡና መጠን ቀደም ካለው ጊዜ አንጻር በ196 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።

በመጪዎቹ ዓመታት ቻይና ከአፍሪካ የግብርና ምርቶችን በስፋት እንደምታስገባም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም