ለሁሉም ክፍት የሆነ የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ይጀመራል

144

ጥር 12/2014/ኢዜአ/ ለሁሉም ክፍት የሆነ የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

የፌዴሬሽኑ የስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ ወይዘሮ ብሩክታዊት አገኘሁ፤ የቴኒስ ውድድሩ ሁሉን አሳታፊ ሆኖ ይከናወናል ብለዋል።

ውድድሩ በታዳጊዎች፣ በአዋቂዎች፣ በአካል ጉዳተኞችና በቀድሞ ተወዳዳሪዎች በሚል በአራት የተለያዩ ካታጎሪዎች ተከፍሎ እንደሚካሄድም ገልጸዋል።

ለሁሉም ክፍት የሆነና የነጠላ ውድድር በመሆኑ በክለብ በሚደረጉ ውድድሮች ተሳትፎ ያላገኙ ስፖርተኞች የውድድር እድል እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል።

ፌዴሬሽኑ በዚህ ውድድር የሚካፈሉ ስፖርተኞችን ሲመዘግብ መቆየቱን ገልጸው በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል የፊታችን ቅዳሜ የሚጀመር ሲሆን ለአራት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

ለውድድሩ አሸናፊ ስፖርተኞች የገንዘብና የአይነት ሽልማት ይጠብቃቸዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም