ህዝበ ክርስቲያኑ ጥምቀትን ሲያከብር ቁርሾን በመርሳት አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ሊሆን ይገባል

51

ሀዋሳ፣ ጥር 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) ህዝበ ክርስቲያኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ያለፈውን ቁርሾ በመርሳትና አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ሊሆን ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስገነዘቡ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለጥምቀት በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ሰዎችን በፍቅር እርስ በርስ የሚያስተሳስር በርካታ አኩሪ እሴቶችን የያዘ ነው።

የበዓሉ እሴት ፍቅርን ለማብዛት፣ ወንድማማችነትን ለማጎልበትና እርስ በርስ መተዛዘንን በማጠናከር በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ትልቅ መሳሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል አስገንዝበዋል።

እሴቱን በመንተራስ ያለፈውን ቁርሾ መርሳት በይቅርታ መሻገር እንደሚገባ የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ "በአሉን ስናከብር በፍቅር በመታነጽና አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ሊሆን ይገባል "ሲሉ  ጥሪ አቅርበዋል።   

"እኛ ኢትዮጵያዊያን ከመገፋፋት በመራቅ በአንድነትና በአብሮነት ከተሰለፍን ሀገራችንን ታላቅ ማድረግ አይሳነንም" ብለዋል።

"ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገረን በመርዳት፣ የተራበና የተጠማን በማብላትና በማጠጣት ሊሆን ይገባል" ሲሉ ርእሰ መስተዳደሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም