ሚኒስቴሩ ከአጋር የልማት ድርጅቶች ጋር በመሆን ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የጤና ቢሮ ማቋቋሚያ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

70

ጥር 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስቴር ከአጋር የልማት ድርጅቶች ጋር በመሆን አዲስ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የጤና ቢሮ ማቋቋሚያ የሚሆኑ የ3 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

በጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የተመራ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ ከኤጀንሲዎች እና ከአጋር የልማት ድርጅቶች የተውጣጡ ኃላፊዎች በክልሉ በመገኘት ያለውን የጤና ዘርፍ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

እንደ ዶክተር ደረጀ ገለጻ ክልሉ አዲስ እንደ መሆኑ መጠን ለማቋቋምና ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት በጥራትና በተደራሽነት ለማሻሻል ድጋፉና ቅንጅታዊ አሰራሩ ይጠናከራል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ እና የክልሉ ስራ ኃላፊዎችም ለተደረገላቸውን ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም