የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሙያተኛ ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያን በሙያቸው እንዲደግፉ ኤጀንሲው ጥሪ አቀረበ

88

አዲስ አበባ፣ ጥር 9/2014( ኢዜአ) በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሙያተኛ ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያ የሳይበር ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ የኢትዮጵያ መረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጥሪ አቀረበ፡፡

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሙያተኛ ዳያስፖራዎች የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን  ጎብኝተዋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በዚህ ወቅን ኢትዮጵያ የልጆቿን እውቀት፣የቴክኖሎጂ ክህሎትና ዕምቅ አቅም የምትሻበት ትክክለኛ ጊዜ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

በዚህም የዘርፉ ባለሙያ ዳያስፖራዎች የኢትዮጵያን የሳይበር ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ከኤጀንሲው ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የሳይበር ምህዳር ሰፊና ተለዋዋጭ በመሆኑ የዘርፉ ባለሙያ ዳያስፖራዎች ያላቸውን ልምድና የቴክኖሎጂ እውቀት እንዲያጋሩም ጠይቀዋል።

"የሁሉም ኢትዮጵያዊያን አገር አንድ ናት፤ አገርን በመደገፍ ህልውናን ለማስጠበቅ ደግሞ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው" ብለዋል።

የዘርፉ ባለሙያዎች የሳይበር ደህንነት ማረጋገጥ በሚያስችሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ  እንዲሰማሩም ጥሪ ቀርቧል።  

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር  በመቀናጀት በሳይበር ደህንነት የሰው ኃይል ልማት ላይ እገዛ እንዲያደርጉም እንዲሁ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም