በጋምቤላ ክልል ከ49 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ያካለለ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ይካሄዳል

73

ጋምቤላ ጥር 8/2014(ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል በተያዘው የበጋ ወራት ከ49 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ያካለለ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ እንደሚካሄድ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኮይት ልዑል ለኢዜአ እንደገለጹት የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራው 153 ተፋሰሶችን መሰረት አድርጎ ይካሄዳል።

በዘንድሮው የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ከ250 ሺህ በላይ ሕዝብ እንደሚሳተፍ ተናግረዋል።

"ለልማቱ 495 ሺህ የነፍስ ወከፍ አነስተኛ የእርሻ መሳሪያዎች ወደ ወረዳዎች ይሰራጫሉ" ብለዋል።

በልማቱ ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች በተጓዳኝ ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ምክትል ኃላፊው አስታውቀዋል።

የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራውን በዚህ ወር አጋማሽ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሚገኙበት በመንጌሽ ወረዳ በይፋ ለማስጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን ምክትል የቢሮ ሀላፊው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም