በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዓመቱ ከ44 ሺህ 300 ሄክታር በላይ የተራቆተ መሬት ይለማል

79

አሶሳ ፤ ጥር 03 / 2014(ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተያዘው ዓመት በሚካሄደው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ከ44 ሺህ 300 ሄክታር በላይ የተራቆተ መሬት እንደሚለማ የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ የ2014 የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራ በአሶሳ ወረዳ አፋ ተፋሰስ ውስጥ  ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ባበክር ከሊፋ በወቅቱ  እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት የተፋሰስ ልማትን ጨምሮ በአካበቢ ጥበቃ ለውጥ ተገኝቷል።

ዘንድሮ በክልሉ ከ44 ሺህ 300 በላይ  በላይ ሄክታር የተራቆተ መሬት ይለማል፤ ይህም በህብረተሰቡ ርብርብ  ስኬታማ እንደሚሆን አልጠራጠርም ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው፤ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን  ላይ ያስመዘገብነው ድል በተፈጥሮ ሃብት ላይ መድገም አለብን ብለዋል፡፡

ዛሬ በአሶሳ ወረዳ በተጀመረው የተፋሰስ ልማት ስራ ላይ  የተሳተፉት የግብርና ሚኒስቴር ተወካይ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤሊያስ እንዳመለከቱት፤ የሀገር ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ በምግብ ዋስትና ራስን መቻል ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ የተፈጥሮ ህብት ጥበቃ ስራን በማጠናከር ግድቦቻችን በደለል እንዳይሞሉ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም