ዳያስፖራዎች በአማራና አፋር ክልሎች የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል

58

ታህሳስ 28/2014/ኢዜአ/ ዳያስፖራዎች በአማራና አፋር ክልሎች በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሲያደርጉት የነበረውን ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

ዳያስፖራዎቹ በጉብኝታቸው በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎችን በአካል በማግኘት ያነጋገሩ ሲሆን፤ ውድመት የደረሰባቸውን ተቋማትም ጎብኝተዋል፡፡

በአካባቢዎቹ ያሉ የኢንቨስትመንትና ልማት አማራጮችን በአካል በመገኘት የተመለከቱ ሲሆን፤ ገለጻም ተደርጎላቸዋል፡፡

በተጨማሪም በጉብኝታቸው በሁለቱ ክልሎች ከሚገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችና ተቋማት መልሰው በሚቋቋሙበት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡

ዳያስፖራዎቹ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በዛሬው እለት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም