የአራዳ ክፍለከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 110 ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች አስተላለፈ

157

ታህሳስ 27/2014/ኢዜአ/በአዲስ አበባ ከተማ የአራዳ ክፍለከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 110 ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች አስተላለፈ።

ክፍለ ከተማው ለነዋሪዎች ካስተላለፋቸው 110 ቤቶች መካካል103 የሚሆኑት የመኖሪያ ሲሆኑ 7ቱ ደግሞ የንግድ ናቸው።

ለነዋሪዎቹ የተላለፉት ቤቶች በሕገ-ወጥ መንገድ በተለያዩ አካላት ተይዘው የነበሩ የመንግስት ቤቶች መሆናቸው ታውቋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ፈይሳ፤ ቤቶቹን በማስተላለፍ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላለፈው በቀጣይም መሰል ተግባራትን እናከናውናለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም