የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ስልጣናቸውን ለቀቁ

118

ታህሳስ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ የገባችው ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ስልጣናቸውን እንደለቀቁ የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በጥቅምት ወር አጋማሽ ከሌሎች ከፍተኛ ሹማምንቶች ጋር በወታደራዊ ሃይሉ በቁም እስር ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም