በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

73
ሰመራ ነሀሴ 21/2010 ከጂቡቲ ወደ ሎግያ ከተማ ይጎዝ የነበረ ኤሮትራከር ቦቲ መኪና በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ ባደረሰው አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ማለፉን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መንሰኤ ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ ምክትል ኮማንደር መሃመድ ኑር አደም ለኢዜአ እንደገለፁት አደጋው  ትናንት ከጧቱ ሦስት ሰዓት ላይ የደረሰው ኮድ 3-24164 ተሳቢ 01393-ኢት ኤሮትራከር ቦት መኪና የኋላ ኮሽኔታ እስከ ጎማው ወልቆ በመብረሩ ነው፡፡ መኪናው ከጅቡቲ ነዳጅ ጭኖ ሰርዶ ነዳጅ ማደያ ካራገፈ በኋላ ወደሎግያ ከተማ ሲጓዝ በዱብቲ ወረዳ ሰርዶ ቀበሌ ልዩስሙ ሰርዶሜዳ በሚባል ቦታ ላይ ሲደርስ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በአደጋውም በአካባቢው ውሃ ቀድተው ወደቤታቸው ሲጓዙ የነበሩ አንድ የአካበቢው አርብቶ አደርና የአራት አመት ልጃቸው በጎማው ተመትተው ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል፡፡ በተጨማሪው ውሃ ተጭኖ የነበረ አንድ አህያም በአደጋው ህይወቱ አልፏል፡፡ አሽከርካሪዎች በተለይም ረዥም ርቀት የሚጓዙ አሸከርካሪዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ወገኖች ደህንነት ሲባል በየጊዜው የተሸከርካሪያቸውን ደህንነት የማረጋገጥ ልምድ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የሟቾቹ አስክሬን ወደቤተሳባቸው የተላከ ሲሆን የመኪናው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም