የአፍሪካ ቀንድ አገራት በሃይል ፍላጎትን የመጫን ድርጊትና ጣልቃ ገብነት አይቀበሉም

63

ታህሳስ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአፍሪካ ቀንድ አገራት በሃይል ፍላጎትን የመጫን ድርጊትና ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበሉ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ገለጹ።

አገራቱ የራሳቸውን ችግሮች በራሳቸው የመፍታት አቅም አላቸው ብለዋል።

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል “በአፍሪካ ቀንድ የኛ ፍላጎትና ሀሳብ የመጨረሻ ቃል ስለሆነ መፈጸም አለበት በሚል ሕገ ወጥ በሆነ መልኩና ሃይል በመጠቀም በሉዓላዊ አገራት ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ጊዜው ያለፈበትና ሕዝባዊ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ውስብስብ የሆኑ ችግሮች ቢኖሩበትም ቀጠናው የራሱን ችግር በራሱ የመፍታት የፖለቲካ ፍላጎት፣ጥበብና አቅም አለው፤ይህንን ማድረግ እንደሚችል በጊዜ ሂደት ያሳያል ብለዋል።

ሁላችንም ጣልቃ ገብነትን በቃ ልንል ይገባል ብለን ድምጻችንን ከፍ አድርገን ልናሰማ ይገባል ሲሉ ነው የማስታወቂያ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተናገሩት።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም