ዳያስፖራው የተለያዩ መረጃዎች የሚያገኝበት ማዕከል ወደ ስራ ገባ

67

ታህሳስ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ዳያስፖራው የተለያዩ መረጃዎችን የሚያገኝበት አዲስ የዳያስፖራ ማዕከል ወደ ስራ ገባ።

ማዕከሉን ወደ ስራ የማስገባት ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን በስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና የዳያስፖራ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ማዕከሉ የበዓል ቀናትን ጨምሮ ከእሁድ እስከ እሁድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በኢኮኖሚው መስክ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የተመለከቱ መረጃዎችን ለዳያስፖራው ተደራሽ የሚያደርግ ነው።

ማህበራዊ ኑሮን የሚያሻሽሉ ስራዎችን በተመለከተ መረጃዎች የሚያገኙበት ስርዓት መዘርጋቱንም ለማወቅ ተችሏል።

በማዕከሉ የአንድ መስኮት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ወሳኝ ኩነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎትም ዳያስፖራው የሚያገኝ ይሆናል።

ዳያስፖራውን በተመለከተ ስለተዘጋጁ ልዩ ልዩ ሁነቶችም በማዕከሉ ገለፃ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም