በታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት የሚጓዙ የዳያስፖራ አባላትን የሚያስተናግድ ዌብሳይት ይፋ ሆነ

197

ታህሳስ 18 ቀን 2014 (ኢዜአ)በታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ መሰረት ወደ የኢትዮጵያ የሚጓዙ የዳያስፖራ አባላትን የሚያስተናግድ ዌብሳይት ይፋ ሆነ።

አንድ ሚሊየን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በርካታ የዳያስፖራ አባላት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት ጉዳዩን እንዲያስተባብር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ሴክሬታሪያትና አስተባባሪ የሆነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የዳያስፖራውን የቆይታ ጊዜ የተቀናጀ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ እንዲሁም ለዳያስፖራው ሁለገብ መረጃ የሚያቀርብና የዳያስፖራ አባላትን መረጃዎች ለማሰባሰብና ለማደራጀት የሚያስችል ወጥ የሆነ የኦንላይን የመረጃ ድረ-ገጽ አዘጋጅቷል።

የድረ-ገጹ አድራሻም www.greatethiopianhomecoming.org ነው፡፡

የዳያስፖራ አባላት በድረ-ገጹ register በሚለው ታብ በመግባት በሚያገኙት ፎርም እንዲመዘገቡ ኤጀንሲው እየጠየቀ፤ ከድረ-ገጹ መረጃዎችን ማየትና ያሏቸውን ጥያቄዎች በመጻፍ ቀጥተኛ ምላሽ ማግኘት እንደሚችሉም ገልፅዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ