የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአምባሳደር ካሳ ከበደ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ

59

ታህሳስ 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአምባሳደር ካሳ ከበደ (ዶ/ር) ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ።

አምባሳደር ካሳ ከበደ (ዶ/ር) ትናንት ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአምባሳደሩ ሞት እጅግ ማዘኑን ገልጿል።

አምባሳደር ካሳ በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ኢትዮጵያን በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ማገልገላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

ሚኒስቴሩና ሰራተኞቹ ለአምባሳደሩ ቤተሰቦች፣ ጓደኞችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም