አየር መንገዱ ከአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን የፋርሚሲቲካል ሎጅሰቲክስ ሽልማትን ተቀበለ

68

ታህሳስ 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአፍሪካ ትልቁ የአቪዬሽን ኢንዳስትሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን በሎጂስቲክስ ዘርፍ የላቀ የሰርተፍኬት ሽልማትን ከዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ተቀበለ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ሽልማቱ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የፋርማሲዩቲካል ማጓጓዣ እንዲኖር ያደርጋል ።

በብራስልስ፣ ሻንጋይ፣ ጆሃንስበርግ፣ ፓሪስ፣ ሴኡል፣ ሌጎስ፣ ሉሳካ፣ ቤጂንግ፣ ሆንግ ጨምሮ ኮንግ፣ ማስትሪችት፣ ቺካጎ እና አዲስ አበባ በሚደረጉ የአቅርቦት ግብ የበለጠ እንደሚያሻሽልም ገልጿል አየር መንገዱ፡፡

የምስክር ወረቀቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም “ይህን ጠቃሚ ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት በማግኘታችን በጣም ደስተኞች ነን" ብለዋል።

የምስክር ወረቀቱ በአቪዬሽን ውስጥ ካሉት የሎጂስቲክስ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የአለም ደረጃዎች ውስጥ አንዱ ጠንካራ ማረጋገጫ ነው” ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው ከአንድ ሚሊዮን ቶን በላይ ዓመታዊ አቅም ያለው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት እና በአዲስ አበባ የሎጂስቲክስ ማዕከል እንደ ፋርማ እና ላይፍ ያሉ ልዩ ልዩ የካርጎ ማስተናገጃዎች አሉት ነው ያሉት፡፡

በዚህም መሰረት አለም አቀፍ ደረጃዎችን ለማሟላት በፋርማሲ እና ላይፍ ሳይንስ አያያዝ ተቋማችን ላይ ጠንክረን እየሰራን ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሽልማቱ የተገኘው የኢትዮጵያ የካርጎ እና ሎጅስቲክስ ቡድን የ ኮቪድ-19 ክትባቶች በአለም ዙሪያ እና በተለይም በአፍሪካ አህጉር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ባለበት መሆኑ ደሞ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል አቶ ተወልደ፡፡

-አካባቢህን ጠብቅ፣ _

ወደ ግንባር ዝመት፣ _

መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም