አሸባሪው ደሴ ከተማን በመውረር በቆየባቸው ጊዜያት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ግፍ ፈጽሟል

84

ደሴ ፤ ታህሳስ 15/2014(ኢዜአ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን የደሴ ከተማን በወረራ ይዞ በቆየባቸው ጊዜያት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ግፍና በደል ፈጽሟል ሲሉ የከተማዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሰይድ የሱፍ ገለጹ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ ልኡክ አሸባሪው ቡድን በደሴ ከተማ ያደረሰውን ውድመት ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው።

የከተማዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የሽብር ቡድኑ ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች የአገልግሎት መስጫዎችን ምህረት አልባ በሆነ መንገድ ሙሉ በሙሉ ዘርፏል፤ ያልቻለውን አውድሟል።

ቡድኑ ይህንን ጨምሮ በከተማዋ  በቆየባቸው ጊዜያት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ግፍና በደልፈፅሟል ብለዋል።

የወደሙ ተቋማትን በጠንካራ ቅንጅት በመጠገን መልሶ ለመቋቋም ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልኡክ የደሴ ቲሹ ካልቸር፣ ወሎ ዩኒቨርሰቲ ደሴ ካምፓስና ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የጎበኙ ሲሆን መረሃ ግብሩ እንደቀጠለ ነው።

ከምልከታው በኋላ  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መልሶ በማደራጀት  ዙሪያ  ከአስተዳደሩ አመራሮች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

በመረሃ ግብሩ ላይ   የፌደራል፣ የክልልና የደሴ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም