ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሰንጋዎች አበረከተ

226

ታህሳስ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሰንጋዎችን አበረከተ፡፡

በዚሁ ወቅት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ድጋፉ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ በመጀመሪያው ዙር ለአገር መከላከያ ሠራዊት 60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰው፤ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በግንባር ከመከላከያና ሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን አኩሪ ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በተለይም አሸባሪውን ህወሓትና ተላላኪውን ሸኔን በመደምሰስ ሀገርን የማዳን ሥራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።