ልዑክ ቡድኑ ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ይዞ ሰመራ ገብቷል

61

ሰመራ፣  ታህሳስ 12 /2014 ( ኢዜአ) በሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር የተመራ ልኡክ ቡድን በአፋር ክልል በጦርነቱ የተጎዱ ጤና ተቋማትን ስራ ለማጀመር ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ገብቷል።

የሃረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ድጋፉን ይዘው ዛሬ ሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሃንፈሬ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በርእሰ መስተዳደሩ የተመራ ልዑክ በአሸባሪው ህወሀት በአፋር ጉዳት ለደረሰባቸው ጤና ጣቢያዎች ስራ ማስጀመሪያ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለማድረግ ነው ሰመራ የገባው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም