በሀገራዊ ጉዳይ የምክክር መድረክ በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

88

ጅግጅጋ ፤ ታህሳስ 9 ቀን 2014 (ኢዜአ) "የኢትዮጵያ ሰላም ፖሊሲና ለሀገራዊ መግባባት መጎልበት የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

የሰላም ሚኒስቴር ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የምክክር መድረኩ ዓላማ  የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የተለያዩ አዳዲስ ሃሳቦችን የማመንጨት፣ የመተንተን፣ የማሰራጨት እና ማህበረሰቡን የማንቃት ሚና  ለማጎልበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ለብሔራዊ መግባባት እና ለሀገራዊ አንድነት የሚያግዙ ምክክሮችን በማካሄድ ምሁራን ሚናቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻልም እንዲሁ።

በመድረኩ ለብሔራዊ መግባባት መጎልበት የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ  እና የኢትዮጵያ የሰላም  ፖሊሲ"  በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ በምሁራን  ጽሁፍ ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡

ዛሬ በተጀመረው የምክክር መድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ፣ የምስራቅ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች፣የሱማሌ ክልል እና የአጎራባች አካባቢዎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም