ዶክተር ሊያ ታደሰ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ለሚገኙ ዳያስፖራዎች ምስጋና አቀረቡ

74

አዲስ አበባ፣ ታህሳሥ 9/2014 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በማሰባሰብ እየተረባረቡ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ምስጋና አቀረቡ።

ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው "በእናንተ እና ኢትዮጵያን በሚወዱ ሁሉ እገዛ የተጎዱ እና የወደሙ የጤና ተቋሞቻችንን ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሰን እንደምንገነባ አልጠራጠርም" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በካናዳ ኦቶዋና ካግላሪ የሚኖሩት የህክምና ባለሙያዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት የመግባት ያደረጉትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የተለያዩ መድሃኒቶችን ይዘው መግባታቸው ይታወሳል።

-አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም