ኢትዮጵያዊያን ከተባበርን የማንሻገረው ወጀብ፤ የማናልፈው መከራ የለም

175

ታህሳስ 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ለዚህም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን የእርዳታ እጆቻቸውን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አዙረዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ክፍለ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረስ ደሴ ተገኝተዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት አቶ ሞላ ተመስገንና አቶ አቶ ጌታቸው ይርዳው ለደሴ ተፈናቃዮች 850 ሺህ ብር የሚያወጣ በቆሎና አልባሳት ድጋፍ ይዘው መምጣታቸውን ይናገራሉ።

ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ ከተዋደድንና ከተረዳዳን የማይቻለን ነገር የለምም ብለዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰይድ እሸቱ ኢትዮጵያውያን የደሴ ተፈናቃዮች ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ያደረገው ድጋፍም የኢትዮጵያዊነቱ ማሳያ ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም ባንኮች ዝግ በመሆናቸው ጭምር  በገንዘብ እጦት የሚሰቃዩ ወገኖች ስላሉ ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።