አሸባሪው ህወሃት በሴቶችና ህፃናት ላይ እየፈፀመ ያለውን ኢሰብዓዊ ጥቃት የሚቃወም ሰልፍ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው

76

ሀዋሳ፣ ታህሳስ 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በሴቶችና ህፃናት ላይ እየፈፀመ ያለውን ኢሰብዓዊ ጥቃት የሚቃወምና የአንዳንድ ምዕራባዊያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ክልል አቀፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሰልፋን እያካሄዱ ያሉት ከተለያዩ ማህበራዊ መሰሠረቶች የተውጣጡ ሴቶች ሲሆኑ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህርላ አብዱላሂ፣ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ተወካይ ወይዘሮ እመቤት ኢሳያስ እና ሌሎች  አመራሮች ተገኝተዋል።

በሰልፉ ላይ "ጾታዊ ጥቃትን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም ይቁም፣ በአሸባሪው ህወሃት በህፃናትና ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት ይቁም፣ እኛም ዝም አንልም፣ ችግራችንን እኛው መፍታት እችላለን፣ እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ" የሚሉና ሌሎች አሸባሪው ህወሃት የሚያደርሰውን ሰብዓዊ ጥቃት የሚቃወሙና የአንዳንድ ምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዙ መፈክሮች እየተሰሙ ነው።

በተለይም አሸባሪው ህወሃት ወረራ በፈጸመባቸው የአማራና የአፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በንፁሀን ሴቶችና ህፃናት ላይ እየፈፀማቸው ያሉ ጭካኔ የተሞላባቸው ኢሰብዓዊ ጥቃቶችን በጽኑ አውግዘዋል።

እንዲሁም አሜሪካና አንዳንድ ምዕራባዊያን እያራመዱ ያሉትን ፀረ-ኢትዮጵያ አቋምና ሚዛናዊነት የጎደለው ጣልቃ ገብነት የሚያወግዙ መልእክቶች እየተላለፋ ይገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም