በመዲናዋ የሚኖሩ የባሶ ሊበን ወረዳ ተወላጆች ለመከላከያ ሰራዊቱ ከ500 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

134

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07/2014(ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የባሶ ሊበን ወረዳ ተወላጆች በጋሸና ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ከ500 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፍን በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በኩል ለሰራዊቱ እንዲደርስ አስረክበዋል፡፡

የድጋፉ አስተባባሪ አቶ አማረ ጥበቡ ሁሉም በተሰማራበት መስክ ለኢትዮጵያ ህልውና የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ድጋፉ የተሰበሰበው ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሆነና በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ተወላጆችን በማስተባበር መሆኑንም ነው የገለጹት።

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ለሰራዊቱ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሁሉም ዜጋ ለኢትዮጵያ ህልውና እና ሉዓላዊነት መጠበቅ ሚናውን በተግባር እንዲወጣም ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ከዚህ አኳያ የደቡብ ጎንደር ዞን ነዋሪዎች ለሰራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት በተግባር እያሳዩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም