አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ በንጹሃን ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት የሚቃወም ሰልፍ በሐረር እየተካሄደ ነው

75

ሐረር፤ ታህሳስ 7 ቀን 2014(ኢዜአ) ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ በንጹሃን ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሐረሪ ክልል ከተማና ገጠር የሚኖሩ ሴቶች ተሰባስበው አደባባይ በመውጣት እያካሄዱት ባለው ሰልፍ  በአሸባሪ ቡድኖቹ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጽመውን  ግፍ በማውገዝ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።

"የኔ እናት ጥቃት ሲደርስባት ዝም አልልም፣  የኔ ልጅ እና እህት ጥቃት ሲደርስባቸው ዝም አልልም" "መሪዋ የዘመተላት ኢትዮጵያ እኔም አለሁላት፣ እኛ ሴቶች ጀግና እንወልዳለን ጀግና እናዘምታለን" ሲሉም መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም፣  የውጭ ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን እያሰሙ ነው።

በሰልፍ ላይ ሴት አመራሮችና በተለያየ አደረጃጀት የሚገኙ ጨምሮ በርካታ ሴቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም