አሸባሪው ህወሃት በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል

117

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት ሁሉም እንዲረባረብ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ፤ በሰጡት መግለጫ አሸባሪው ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአማራ እና አፋር ክልሎች በርካታ የመሰረተ ልማቶችን ዘርፏል፣ አውድሟልም ብለዋል።

ቡድኑ ያወደማቸውና የዘረፋቸው የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለመልሶ ግንባታ የቢሊዮን ብሮችን ወጪ ይጠይቃሉ ብለዋል።

በመሆኑም አሸባሪው ህወሃት ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት መላ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲረባረቡ ጠይቀዋል።

አሸባሪው ህወሃት በወረራ በገባባቸው የአማራና አፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች ማህበራዊ ተቋማትን ከመዝረፍ በተጨማሪ በርካታ ንጹሃንን በመግደል፣ ሴቶችን በመድፈርና የተለያዩ ንብረቶችን በመዝረፍና በማውደም ጭምር አረመኔያዊ ድርጊቶችን ፈጽሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም