አራት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በጥምረት የፕላስቲክ ብክለትን ለማስቀረት ተስማምተዋል

244

ታህሳስ 4/2014/ኢዜአ /አራት የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የሆኑት ታንዛኒያ ፣ኬኒያ፣ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ በጥምረት የፕላስቲክ ብክለትን በቀጣናቸው ለማስቀረት ተስማምተዋል፡፡

አራቱ ሀገራት ከፕላስቲክ የፀዳ የምስራቅ አፍሪካ ኮሚኒቲ እንዲኖር እንደሚሰሩ ተገልፆ፤ይህም ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይችሉ  ፕላስቲኮችን ያለመጠቀም ዘመቻን አስጀምረዋል፡፡

“ጊቭ ሚ ዘ ብሩም “ የተሰኘ ንቅናቄም በታንዛኒያ  ቀጣይነት ያለው እድገትን  ለማምጣት የአካባቢ ብክለትን ለማስቀረት ግንዛቤ የሚፈጥር ድርጅት ነው ፡፡

የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ሊ ሮቻ በሰጡት መግለጫ ዘመቻው በአራት ድርጅቶች ድጋፍ እተካሄደ መሆኑን ገልፀው  ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይችሉ የፕላስቲክ ምርቶች መመረት እንዲያቆሙና የፕላስቲክ ብክለት የቀጣናው ችግር እንዳይሆን መስራት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ሩዋንዳ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይችሉ ፕላስቲኮችን ጥቅም ላይ ባለማዋል ስኬታማ ስትሆን ኬኒያ ይህን ጥሰው በሚገኙም ከባድ ቅጣት በመጣል ትታወቃለች፡፡

ሮቻ እንዳሉት የምስራቅ አፍሪካ ኮሚኒቲ ሃገራት ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይችሉ ፕላስቲኮችን ባለመጠቀም  ለአለም ምሳሌ ለመሆን  እንደሚሰሩም ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም