ታሪካዊቷ የደሴ ከተማ ከትላንት ምሽት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝታለች

52

ታህሳስ 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) ታሪካዊቷ የደቡብ ወሎ ዞን መቀመጫ የሆነችው የደሴ ከተማ ከትላንት ምሽት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

አሸባሪው ህወሓት ወደ ከተማዋ ሰርጎ ከገባበት ጊዜ ጀመሮ ኤሌክትሪክ አጥታ የቆየችው ታሪካዊቷ ደሴ የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማኔጅመንትና የቴክኒክ ሰራተኞች ባደረጉት ጠንካራ ርብርብ ትናንት ማታ በድጋሚ ኤሌክትሪክ አግኝታለች ነው ያለው።

የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ ሁሉም ሰራተኞች ወደ ቀየው የተመለሰውን ህብረተሰብ በጨለማ እንዳይሰቃይና ኑሮው እንዲቀልለት ለማድረግ በትጋት እየሰሩ ይገኛሉም ብሏል።

በትናንትናው ዕለት የኢንዱስትሪ ማዕከል የሆነችው የኮምቦልቻ ከተማም አመሻሽ ላይ የኤሌትሪክ አገልግሎት ማግኘቷ ይታወቃል።

ነፃ የወጡ ሌሎች አካባቢዎች ላይ የተጉዱና የወደሙ የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመሮች የመጠገንና የመገንባት ስራ በእልህና በወኔ በመስራት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙና ከጨለማ እንዲላቀቁ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ አየተሰራ ይገኛል ሲል የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም