ዓብይ እና ፓን-አፍሪካኒዝም

79

በእስሌማን አባይ

አፍሪካ በፀጥታው ምክር-ቤት የሚገባት ቋሚ መቀመጫ


የፀጥታው ምክር ቤት አራቱን የሁለተኛው የአለም ጦርነት አሸናፊዎች ማለትም አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ እና ቻይና በቋሚ አባልነት እና በየሁለት አመቱ የሚቀያየሩ አስር ተለዋጭ አባላትን ይይዛል፡፡ ይህ ምክር ቤት ከሰላም እና ከደህንነት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከፍተኛው የድርጅቱ ክንፍ በመሆኑ ማዕቀቦችን ይጥላል፣ የሀይል እርምጃዎችን ያፀድቃል ወይንም ይሽራል፡፡ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የዘጠኝ አባላት ድምፅ ሲያስፈልግ የቋሚ አባላቱ ሙሉ የስምምነት ድምፅ ግን የግድ ያስፈልጋል፡፡

አምስቱ አገሮች በሞኖፖል ጠቅልለው በያዙት ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ውሳኔዎች እንዲያልፉ ወይም እንዲወድቁ ድምፅ የሚሰጡት ከአለም አቀፍ ህግ በመነሳት ሳይሆን፣ ከራሳቸው መንግስት ጥቅም እና ፍላጎት አንፃር ነው። የፀጥታው ምክር ቤት የተቋቋመው አለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነትለ ለማስከበር ቢሆንም እያገለገለ ያለው ግን ለየአገሮቹ የኢኮኖሚ ጥቅም እና የጡንቻ ብቃት መለኪያነት ነው፡፡

በአለም ላይ ያሉ አገሮችና ህዝቦች እጣፈንታ በአምስት አገሮች ፍላጐት እንዲወሰን በመፈቀዱ ምክንያት አለማችን ይሆናሉ ተብለው የማይገመቱ እልቂቶችንና አሳዛኝ ክስተቶችን እንድታስተናግድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የሩዋንዳው እልቂት፣ የዳርፉር እና የሶሪያ ሰብአዊ ቀውሶች እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ። የመንግስታቱ ድርጅት ሩዋንዳ ውስጥ የተከሰተውን የዘር ማጥፋት እልቂት ቀድሞ መከላከል ያልቻለው ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ባላቸው አሜሪካን እና ፈረንሳይ ውሳኔ ነው፡፡ ሁለቱ አገሮች ከየጥቅሞቻቸው በመነሳት፡- አሜሪካ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ፣ ፈረንሳይ ደግሞ አጋሮቿን ላለማጣት በሚል የግል ስሌት ውስጥ በመግባታቸው ነው … ብዙሀን በአደባባይ እንደ በግ የታረዱት።

በተመድ ጉባዔዎች 50 በመቶው አጀንዳ የአፍሪካ ጉዳይ ነው። የህብረቱ ከ 25 በመቶ በላይ አባላት የአፍሪካ አገራት ናቸው። ይሁን እንጂ የተመድ አካል የሆነው የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካን መቀመጫ እንደነፈገ ይገኛል። ምክር ቤቱ ሲቋቋም ቅኚ ገዢ አገራት በዛኔው አቋማቸው ያዋቀሩት ነው። በቅኚ አገዛዝ ዘመን በተጀመረ አሰራር ዛሬ ድረስ እየተኬደ የአፍሪካ ፍላጎት እንዴት ቅቡላዊ ይሆናል? እጣ ፋንታዋን ምዕራቦች እያሰመሩላት የምትቀጥለውስ እስከመቼ?

አፍሪካ ቋሚ መቀመጫ ይኑራት የሚሉ ድምፆች መሰማት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አፍሪካዊ ያልሆኑ አገራትም ምክር ቤቱ ኢ-ፍትሃዊ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። አፍሪካ ሁለት ቋሚ አባል አገራት የ veto ስልጣን ጋር እንዲሁም ሌሎች መቀመጫዎችም ይገባታል የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ እየተነሳ ያለ ነው።

አፍሪካ፤ ጃፓን፤ ህንድ እና የብሪክስ አገሮች የፀጥታው ምክር ቤት አሰራር ላይ የማሻሻያ ለውጥ እንዲደረግ ከሚጎተጉቱ አገሮች እና አካባቢያዊ ድርጅቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ አሁን ባለው አሰራር የብዙሀንን ጥቅም ማስከበር እንደማይቻል በተለያዩ ማስረጃዎች አስደግፈው ያቀርባሉ።

የመንግስታቱ ድርጅትን በዋና ፀሀፊነት ካገለገሉ ሰዎች ውስጥ ለውጥ እንደሚያሻ ተናግረው የማያውቁት አንዱ ብቻ ናቸው፡፡
ከአፍሪካ ውጪ ያሉ ተቋማት አገራትና ምሁራንም አፍሪካ ቋሚ መቀመጫ እንደሚገባት ደጋግመው ጠይቀዋል።

2005 እኤአ
የአፍሪካ ህብረት በፀጥታዉ ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲሰጠው በ 2005 እኤአ መጠይቁ ይታወቃል።


ህብረቱ በአዲስ አበባ ባካሄደዉ ጉባኤው ተመድ ከጀርመን፤ ከጃፓን፤ ከህንድና ከብራዚል የቀረበለትን የቋሚ መቀመጫ ጥያቄ ተቀብሎ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ግን አትጠይቁ በማለት ዉድቅ ማድረጉ የሚታወቅ ነዉ።

ምክንያቱ አምስቱ የጸጥታዉ ምክር ቤት አባላት ማለትም ዩናይትድ ስቴትስ፤ ፈረንሳይ፤ብሪታንያ፤ ቻይናና ሩሲያ ይህን መሰሉን ሃይላቸዉን ያለተቀናቃኝ ይዘዉ መዝለቅ ስለሚፈልጉ ነው ተብሎም ነበር።

አፍሪካ ህብረት ባቀረበዉ ረቂቅ ሰነድ ላይ ታዲያ በፀጥታ ምክር ቤቱ የሚገቡት አዲስ ቋሚ አባላት እንደነባሮቹ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብትን ጨምሮ ተመሳሳይ የሆነ ስልጣንና ጥቅም ሊሰጣቸዉ ይገባል ይላል።

የአፍሪካ የልማት ተቋም ዳይሬክተር ኩዋሜ አክኖር በበኩላቸዉ የፀጥታ ምክር ቤቱን የማስተካከሉ ነገር መሰታዊ የሆነዉን የስልጣን መዋቅር የማይነካ ከሆነ ምን ትርጉም አለዉ? ሲሉ ይጠይቃሉ። አያይዘዉም ድምፅን በድምፅ የመሻር ስልጣን ለዓለም ዓቀፍ ፓለቲካ ዋነኛ መሳሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ከገለፁ በኋላ የአፍሪካ ህብረት ይህን ስልጣን አዲስ አባላት እንዲጋሩ ያቀረበዉን ጥያቄ ሊገፋበት ይገባል ብለዋል።

በወቅቱ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ ኮፊ አናን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህን እናደርጋለን ብሎ ማለት ከሃሳብ እንደማይዘል ግልፅ አድርገው ነበር። ምክንያቱንም ሲያብራሩ በርካታ አባል አገራት ድምፅን በድምፅ የመሻር ስልጣን ያላቸዉ አገራት ቁጥር እንዲበረክት ይሻሉ ነገር ግን እነዛ ይህን ስልጣን የተቆጣጠሩት አገራት ሌላ ተጨማሪ እንዲመጣባቸዉ ስለማይፈልጉ ሲሉ ነገሩን ግልፅ አድርገዉታል።

የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርቶ ሙጋቤ አዲስ አበባ በፈረንጆቹ 2016 በተካሄደው 26ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተመድ የጸጥታው ም/ቤት ማሻሻያ እንዲያደርግ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡
ሙጋቤ በህብረቱ ጉባኤ ላይ ለተገኙት የተመድ ዋና ጸኃፊ ባን ኪሙን ነበር ም/ቤቱ ማሻሻያ እንዲያደርግ የተናገሩት፡፡

ሩሲያ 2017
ሩሲያ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ድጋፍ እንደምታደርግ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ መናገራቸው የሚታወስ ነው። ላቭሮብ በየካቲት 2010 ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ተገኝተው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፈቂ ማህማት ጋር በአህጉራዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ባደረጉት ውይይት ላይ ነበር ሩሲያ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እንደምትሰራ የገለፁት። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሚደረገው ማሻሻያ አፍሪካን ያካተተ ሊሆን እንደሚገባም ነው የተናገሩት።
2016
አምስተኛው የጣና ከፍተኛ የአፍሪካ የደኅንነት ምክክር መድረክ ባህር ዳር ከተማ ላይ በሚያዝያ 2016 የቀድሞው የተመድ ዋና ጸሐፊና የኖቤል ሽልማት አሸናፊው ኮፊ ኦናን ባደረጉት ንግግር አፍሪካ በዓለም አቀፍ የደኅንነት አጀንዳዎች ላይ የተሻለ ቦታ ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ተገቢ እንደሆነ አስምረውበታል፡፡
አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራና ወጥ የሆነ ድምፅ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሊኖራት ይገባል ሲሉም ተከራክረዋል፡፡

በሙኒክ የደኅንነት ኮንፈረንስ ሊቀመንበሩ ወልፍጋንግ ኢስችንገር ንግግርም ተስተጋብቷል፡፡ ‹‹አፍሪካ በዓለም አቀፍ አስተዳደራዊ ተቋማት ውስጥ የተሻለ ውክልና ለማግኘት ያላት ዕቅድ በእኔ እምነት ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ወንበር ሊኖራት ይገባል፡፡ ከቋሚ አባላቱ ውስጥ የአፍሪካን ውክልና አንዱ የማድረግ ጥያቄ እንደውም እንደዘገየ ነው የማስበው፡፡ የአውሮፓ ኅብረት ለዚህ ዕቅድ ሙሉና የማያወላዳ ድጋፍ ሊሰጥ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ካርሎ ሎፔዝ በበኩላቸው፣ በርካታ ዓለም አቀፋዊ የደኅንነት አጀንዳዎች ላይ አፍሪካውያን የመገለል ስሜት ይሰማቸዋል ብለው ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም