የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ሊካሄድ ነው

53
ሐረር ነሀሴ18/2010 የሐረሪ ክልል  ምክር ቤት አምሰተኛው ዙር ሶስተኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ነሐሴ 23/2010ዓ.ም እንደሚጀመር የክልሉ ምክር ቤት  ጽህፈት ቤት ገለጸ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ ዛሬ ለኢዜአ እንዳሉት  ምክር ቤቱ ለሶስት ቀናት በሚያደርገው ጉባኤው የክልሉን የ2010 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ቀርቦ ውይይት ይካሄዳል። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2010 የስራ ሪፖርት ለምክር ቤቱ እንደሚቀረብ ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም የ2011 በጀት ዓመት የስራ ዕቅድ ፣ የወረዳ ምክር ቤት የምርጫ ማራዘሚያ እና የፋይናንስ አስተዳደር ፣  በጀት ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም