አንዳንድ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ተጠየቀ

104

ሆሳዕና ፤ ህዳር 30/2014(ኢዜአ) አሜሪካ ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ተጠየቀ።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ  ማህበረሰብ በቃ /#No More" / የንቅናቄ ዘመቻን መቀላቀላቸውን በአደባባይ ባካሄዱት ሰለማዊ ሰልፍ አስታውቀዋል።

እነዚህ የተቋሙ ተማሪዎች፣መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በሰልፋቸው አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት በጽኑ አውግዘዋል።

በተጨማሪም የእነዚህ ሀገራት የመገናኛ ብዙኃን ሐሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት እንዲታቀቡም ጠይቀዋል።

አሸባሪውና ወራሪው ህወሓት በፈጸመው ወንጀል ለፍርድ እንዲቀርቡም እንዲሁ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ፤  ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት እንደሌለውና እንደማይሳካ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን የእነሱን የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ አስተሳሰብ አንቀበልም ያሉት ዶክተር ሀብታሙ፤ እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱም ጠይቀዋል።

በዩኒቨርሲቲው የምህንድስናና ቴክኖሎጂ መምህር አቶ ታምራት ፍቅሬ  በሰጡት አስተያየት። አሸባሪውን ህወሓት በመደገፍ በኢትዮጵያ ጫና ለማሳደር የሚንቀሳቀሱትን አሜሪካ ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራትን  ለመቃወም ሰልፉን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳት ጣልቃ መግባት ተቀባይነት ስለሌለው እጃቸውን እንዲያነሱ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘረኛውና ከፋፋዩን ቡድን በመፋለም የሀገሩን ህልውና ለማስጠበቅ ወደማይፈለገው ጦርነት መግባቱን መረዳት ይገባቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡት አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራትና የሐሰት መረጃ የሚያሰራጩት መገናኛ ብዙኃኖቻቸው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የጠየቀው ደግሞ የዩኒቨርሲቲው የሦስተኛ ዓመት የቋንቋና ሥነ ጽሁፍ ተማሪው ዳዊት ኮላቶ ነው።

"ኢትዮጵያውያን የአድዋ ልጆች መሆናችንን መረዳት ይገባል''ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል።

በቃ/#No More/  በዓለም ታላላቅ ከተሞች ተጀምሮ በተለያዩ ሀገራት ተቀባይነት እያስገኘ ያለ የንቅናቄ ዘመቻ እየሆነ ይታወቃል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም