ጆ ባይደን ለጉብኝት በመጡበት ካንሳስ ከተማ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን አሰሙ

73

ህዳር 30 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለጉብኝት በመጡበት ካንሳስ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ፕሬዚዳንት ባይደን ሚዙሪ ግዛት በምትገኘው ካንሳስ ከተማ ረቡዕ ከሰዓት የስራ ጉብኝት አካሂደዋል።

በጉብኝቱ ወቅት በከተማዋ የሚገኙ የኢትዮጵያውን ማህበረሰብ አባላትና የትራምፕ ደጋፊዎች ተቃውማቸውን አሰምተዋል።

ተቃዋሚዎቹ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር በሚያካሂደው እንቅስቃሴ ቁጣቸውን እንዳሰሙ የዘገበው ኬኤምቢሲ “በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደውን የውክልና ጦርነት እና ጣልቃ ገብነት እኛ በቃ፣ በቃ እንላለን” ማለታቸውን አስነብቧል።

ተቃዋሚዎች “የጆ ባይድን አስተዳደር አሸባሪው ህወሃትን የመደገፍ እንቅስቃሴውን ሊያቆም ይገባል፣ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ለማጥፋት የሚያካሄደው ጣልቃ ገብነትም ሊቆብ ይገባል” ብለዋል።

በተቃውሞው ተሳታፊ ከነበሩት መካከል ሄኖክ ተከስተ እና ፀደንያ ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት ፤እኛ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ፣ ገለልተኛና ነጻ መንግስት አለን ጣልቃ ገብነቱ እንዲቆም እናሳስባለን” ብለዋል።

በተቃውሞው የተሳተፉት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችም አሜሪካ ከአፍጋኒስታን እንድትወጣ በተላለፈው ውሳኔና የባይደን አስተዳደር የኮቪድ-19 ቀውስን ለመቋቋም በሚሰጠው ምላሽ ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም