በክልሉ የትምህርት ማህበረሰቡን በማስተባበር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ተጀመረ

113

ጋምቤላ ህዳር 27/ 2014 (ኢዜአ) የጋምቤላ ክልል የትምህርት ማህበረሰቡን በማስተባበር ህወሀት በከፈተው ጦርነት በአማራና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ተጀመረ።
ትላንት በተጀመረው መርሀ ግብር ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለማሰባሰብ መታቀዱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለኢዜአ አስታውቋል ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኮንግ ጆክ እንደገለጹት እንደ ሀገር ለአንድ ሳምንት ተማሪዎች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል እንዲሰበስቡ ትምህርት ቤቶች የተዘጉበት ሁኔታ ቢኖርም እንደ ጋምቤላ ክልል ተጠባጭ ትምህርት ቤቶች ሳይዘጉ የሰባዊ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ይካሄደል።

የትምህርት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ተማሪዎችን በማስተባበር ገቢው የሚሰበሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የሰባዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ከጥሬ ገንዝብ በተጨማሪ የደም ልገሳና የጽዳት ስራዎች እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

የክልል የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መረሃ ግብሩን ለማስተባበር በሁሉም ወረዳዎች ስምሪት ተካሄዶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው አስታውቀዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም