ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት መጠበቅ ድጋፍ የሚሰጥና የ’በቃ’ ንቅናቄ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በጣሊያን ቱሪን ከተማ ተካሄደ

84

ህዳር 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉትን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ እና ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት መጠበቅ ድጋፍ የሚገልጽ ሠላማዊ ሠልፍ በጣልያን ቱሪን ከተማ ካስቴሎ አደባባይ ተካሄደ።

በሰልፉ የተሳተፉት ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫናና በየሚዲያዎቻቸው የከፈቱትን የሐሰት ዘመቻ ተቃውመዋል።

የ’በቃ’ ወይም #NoMore አካል በሆነው በዚህ ሰልፍ ምዕራባውያኑ ወገንተኛ አካሄዳቸውን እንዲያቆሙ የሚጠይቁ ሀሳቦችን የተላላፉ ሲሆን የአሸባሪው ህወሃትን የጥፋት ድርጊት የሚያወግዝ እና የኢትዮጵያ መንግስትን አገር የመታደግ እንቅስቃሴ የሚደግፍ መልዕክትም አሰምተዋል።

በአሁኑ ወቅት ያለምንም የፖለቲካ እና የሀይማኖት ልዩነት ስለሀገር ህልውና በአንድነት መቆም እንደሚያስፈልግም ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።በጦርነቱ የተጎዱትን የህብረተሰብ ክፍሎችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ የህዝብ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት በቅርብ ሀብት የማሰባሰብ ስራ እንደሚያካሂዱም ቃል መግባታቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም