ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቬትናም ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

63
አዲስ አበባ ነሐሴ 17/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቬትናም ፕሬዝዳንት ትራን ዳይ ኳንግን አነጋገሩ። ፕሬዝዳንት ኳንግ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገቡት ዛሬ ከቀትር በኋላ ነው። ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ተቀበለዋቸዋል። ትራን ዳይ ኳንግ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ነው። በቆይታቸውም የሁለቱን አገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ሊያሳድጉ የሚችሉ ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያና ቬትናምን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ የቢዝነስ ፎረም ይካሄዳል። ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ ለተመሳሳይ የስራ ጉብኝት ወደ ግብፅ ያቀናሉ። ኢትዮጵያና ቬትናም በይፋ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር መጋቢት 1976 ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም