የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ለመከላከያ ሰራዊት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

55

አዲስ አበባ ፣ህዳር 25/2014(ኢዜአ) የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ እና ተጨማሪ የአይነት ድጋፎችን አደረጉ።

ለህልውና ዘመቻው አሸባሪዎችን እየተፋለመ ለሚገኘው ሰራዊት የተቋማት፣ የማህበረሰቡና የተለያዩ ግለሰቦች ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዛሬው እለትም የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ኢትዮ-ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፣ የወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለሰራዊቱ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርገዋል።

በዚህም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 20 ሚሊዮን ብር እና 20 ሰንጋዎችን እንዲሁም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የስንቅ ድጋፍ አድርጓል።

ቱሪዝም ሚኒስቴር ደግሞ 5 ሚሊዮን ብር እና 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የስንቅ ድጋፍ አድርጓል።

ኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት 224 ሺህ ብር፣ የወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የ100 ሺህ ብር ድጋፍ ለግሰዋል።

በጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን 39 ሺህ ዶላር፣  በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ወርቅነሽ ተፈራ የተባሉ ግለሰብ ከተለያዩ ስዎች ያሰባሰቡትን 100 ሺህ ብር እና 1 ሺህ 50 ዩሮ ለመከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል።

የብሄራዊ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ የክልሎች አስተባባሪ ዶክተር ተመስገን ቡርቃ፤ ድጋፉን የተረከቡ ሲሆን ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  

የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር ዳር በመነሳሳት ለሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍም አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም