"አንድ ሚሊዮን ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተከትሎ የትኬት ሽያጭ በፍጥነት እየተከናወነ ስለሚገኝ የመስተንግዶ ተቋማት ዝግጅት ማድረግ አለባቸው

94

ህዳር 25/2014 (ኢዜአ) “አንድ ሚሊዮን ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የመጓጓዣ ትኬት ሽያጭ በፍጥነት እየተከናወነ ስለሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሆቴሎችና ሌሎች የመስተንግዶ ተቋማት ጥሪውን የሚመጥን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ሲሉ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ “1 ሚሊዮን ሀገር ወዳዶች ወደ ሀገር ቤት በታኅሣሥ 29 /2014 እንዲገቡ በቀረበው ጥሪ መሰረት አገር ወዳድ ወገኖች የአውሮፕላን ትኬት እየገዙ ይገኛሉ” ብለዋል።

አክለውም የትኬት ሽያጭ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ዛሬ ሎስ አንጀለስ ላይ መረዳት ችያለሁ” ነው ያሉት።

“ስለሆነም አየር መንገዳችን፣ ሆቴሎችና ሌሎች የመስተንግዶ ተቋማት ጥሪውን የሚመጥን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው እገልጻለሁ” ሲሉ አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና #የኢትዮጵያ ወዳጆች የ #ወደሀገርቤት እንግባ ጥሪን እንድትቀላቀሉ እንጋብዛለን” ማለታቸው ይታወሳል።

1 ሚሊየን ሰዎች በሀገር ቤት ታኅሣሥ 29፣ 2014 ዓ.ም. ድረስ እንዲገቡም ነው ጥሪ ያቀረቡት።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም