"አሸባሪው ህወሃት በካሳጊታ የገደላቸውን ንፁሃን እንቅበር ብንል እንኳን ከልክሎናል"

70

አዲስ አበባ ህዳር 24/2014(ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በካሳጊታ ወረራ ፈፅሞ በቆየባቸው ጊዜያት በግፍ የገደላቸው ንፁሃን እንዳይቀበሩ በመከልከል አረመኔነቱን አሳይቷል።

አሸባሪው ህወሃት ወረራ ፈፅሞ በቆየባቸው በአፋርና አማራ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በበርካታ ንጹሃን ላይ ግዲያ ፈፅሟል፣ ንብረት በመዝረፍ የተረፈውንም አውድሟል።

የሽብር ቡድኑ በእነዚህ አካባቢዎች ለአይን የሚቀፉና ለጆሮ የሚከብዱ ዘግናኝ ተግባራትን በመፈፀም የአረመኔነት ጥጉንም አሳይቷል።  

የካሳጊታ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሊ በቱ መሃመድ፤ "አሸባሪው ህወሃት በካሳጊታ የገደላቸውን ንፁሃን እንቅበር ብንል እንኳን ከልክሎናል" ብለዋል።

በአሸባሪው በካሳጊታና አካባቢዋ የተፈጸመው ግፍ በሰው ልጅ ላይ ያደረጋል ተብሎ የማይታሰብ "አረመኔያዊ ድርጊት" መሆኑንም ገልጸዋል።

የህወሃት የሽብር ቡድን ንፁሃንን ከመግደልና ንብረት ከመዝረፍ እንዲሁም ከማውደም በተጨማሪ የነዋሪዎችን እንስሳት እያረደ በመብላትም ብዙ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።

አሸባሪው ህወሃት የሃይማኖት ተቋማትን በማውደምና ቅዱሳን መፅሃፍትን በማቃጠል ሃይማኖታዊ ጥላቻውን በተግባር አሳይቷል።

የሽብር ቡድኑ ጭካኔ የታከለበት ጥፋት ህዝብን የመጉዳትና አገር የማፍረስ ዓላማ መሆኑንም በተግባር አይተነዋል ብለዋል አቶ አሊ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ በአውደ ግንባር እየመሩት ባለው "ዘመቻ ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አሸባሪውን በጀግንነት እየተፋለሙት መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም