የወሊሶ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ስራ ተጀመረ

71

ህዳር 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የወሊሶ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ስራ ተጀመረ።

ግንባታውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሣና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ አስጀምረውታል።

ለፕሮጀክቱ ግንባታ 230 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን ገንዘቡም ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር የተገኘ መሆኑም ተገልጿል።

የፕሮጀክቱን ግንባታ GTP የተሰኘ አገር በቀል ድርጅት የሚያካሄድ ሲሆን GEDAG የተባለ አማካሪ ድርጅትም የማማከሩን ስራ የሚሰራ መሆኑም ታውቋል።

ግንባታውም በ1 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታሰቡንና ከ157ሺ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚደርግ መሆኑም ተገልጿል።

አካባቢህን ጠብቅ

ወደ ግንባር ዝመት

መከላከያን ደግፍ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም