ክለቡ ለመከላከያ ሠራዊት 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

83

ሆሳዕና ህዳር 23/2014(ኢዜአ) የሀድያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ አባተ ተስፋዬ ለኢዜአ እንደገለጹት ክለቡ ድጋፉን ያደረገው ከአሰልጣኞች ፣ከተጫዋቾችና ከጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች ጋር ከተወያየ በኋላ ነው።

በውይይቱ በአሸባሪው ህወሓት የተቃጣውን ሀገር የማፍረስ ሴራ ለመመከት ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ውሳኔ ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

በውሳኔው መሰረት የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር፤ ክለቡ ደግሞ 500ሺህ ብር መለገሳቸውን አስታውቀዋል።

 ክለቡ የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አቶ  አባተ አስታውቀዋል።

 የሀድያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም